ሁሉም የእስልምና ቤተ መጻሕፍት

92 - The Night - Al-Layl

:1

በሌሊቱ እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡

:2

በቀኑም፤ በተገለጸ ጊዜ፡፡

:3

ወንድንና ሴትን በፈጠረውም (አምላክ እምላለሁ)፡፡

:4

ሥራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው፡፡

:5

የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፡፡

:6

በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤

:7

ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡

:8

የሰሰተ ሰውማ የተብቃቃም፤ (በራሱ የተመካ)፤

:9

በመልካሚቱ (እምነት) ያሰተባበለም፤

:10

ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡

:11

በወደቀም ጊዜ ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመውም፡፡

:12

ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን፡፡

:13

መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛ ናቸው፡፡

:14

የምትንቀለቀልንም እሳት አስጠነቀቅኳችሁ (በላቸው)፡፡

:15

ከጠማማ በቀር ሌላ የማይገባት የኾነችን፡፡

:16

ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝ የሸሸው፡፡

:17

አላህን በጣም ፈሪውም በእርግጥ ይርቃታል፡፡

:18

ያ የሚጥራራ ኾኖ ገንዘቡን (ለድኾች) የሚሰጠው፡፡

:19

ለአንድም ሰው እርሱ ዘንድ የምትመለስ ውለታ የለችም፡፡

:20

ግን የታላቅ ጌታውን ውዴታ ለመፈለግ (ይህንን ሠራ)፡፡

:21

ወደፊትም በእርግጥ ይደሰታል፡፡