ሁሉም የእስልምና ቤተ መጻሕፍት

91 - The Sun - Ash-Shams

:1

በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡

:2

በጨረቃም በተከተላት ጊዜ፤

:3

በቀኑም (ፀሐይን) በገለጻት ጊዜ፤

:4

በሌሊቱም በሸፈናት ጊዜ፤

:5

በሰማይቱም በገነባትም (ጌታ)፤

:6

በምድሪቱም በዘረጋትም፤

:7

በነፍስም ባስተካከላትም፤

:8

አመጽዋንና ፍርሃትዋንም ባሳወቃት (አምላክ እምላለሁ)፡፡

:9

(ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡

:10

(በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡

:11

ሠሙድ ወሰን በማለፍዋ አስተባበለች፡፡

:12

ጠማማዋ በተንቀሳቀሰ ጊዜ፡፡

:13

ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡

:14

አስተባበሉትም፡፡ (ቋንጃዋን) ወጓትም፡፡ በኀጢኣታቸውም ምክንያት ጌታቸው (ቅጣትን) በእነርሱ ላይ ደመደመባቸው፤ አስተካከላትም፡፡

:15

ፍጻሜዋንም (የምታስከትለውን) አያፈራም፡፡