90 - The City - Al-Balad
:1
በዚህ አገር (በመካ) እምላለሁ፡፡
:2
አንተ በዚህ አገር ሰፋሪ ስትኾን፡፡
:3
በወላጂም በወለዳቸውም ሰዎች (በአዳምና በዘሮቹ ሁሉ እምላለሁ)፡፡
:4
ሰውን ሁሉ በእርግጥ በልፋት ውስጥ ኾኖ ፈጠርነው፡፡
:5
በእርሱ ላይ አንድም የማይችል መኾኑን ይጠረጥራልን?
:6
«ብዙን ገንዘብ አጠፋሁ» ይላል፡፡
:7
አንድም ያላየው መኾኑን ያስባልን?
:8
ለእርሱ ሁለት ዓይኖችን አላደረግንለትምን?
:9
ምላስንና ሁለት ከንፈሮችንም፡፡
:10
ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?
:11
ዓቀበቲቱንም አልወጣም፡፡
:12
ዓቀበቲቱም (መውጣቷ) ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
:13
(እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡
:14
ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡
:15
የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤
:16
ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡
:17
(ዐቀበቲቱን አልወጣም)፡፡ ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች አልኾነም፡፡
:18
እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡
:19
እነዚያም በአንቀጾቻችን የካዱት እነርሱ የግራ ጓዶች ናቸው፡፡
:20
በእነርሱ ላይ የተዘጋች እሳት አልለች፡፡