93 - The Morning Hours - Ađ-Đuĥaá
1
በረፋዱ እምላለሁ፡፡
2
በሌሊቱም ጸጥ ባለ ጊዜ፤
3
ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም፡፡
4
መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡
5
ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡
6
የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)፡፡
7
የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም፡፡
8
ድኻም ኾነህ አገኘህ፤ አከበረህም፡፡
9
የቲምንማ አትጨቁን፡፡
10
ለማኝንም አትገላምጥ፡፡
11
በጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)፡፡