87 - The Most High - Al-'A`lá
:1
ከሁሉ በላይ የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡
:2
የዚያን (ሁሉን ነገር) የፈጠረውን ያስተካከለውንም፡፡
:3
የዚያንም የወሰነውን፡፡ (ለተፈጠረለት ነገር) የመራውንም፡፡
:4
የዚያንም ግጦሽን (ለምለም አድርጎ) ያወጣውን፡፡
:5
(ከዚያ) ደረቅ ጥቁር ያደረገውንም (አምላክ ስም አሞግስ)፡፡
:6
(ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡
:7
አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡ እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም ሁሉ ያውቃልና፡፡
:8
ለገሪቱም (ሕግጋት) እንገጥምሃለን፡፡
:9
ግሣጼይቱ ብትጠቅም (ሰዎችን) ገሥጽም፡፡
:10
(አላህን) የሚፈራ ሰው በእርግጥ ይገሠጻል፡፡
:11
መናጢውም ይርቃታል፡፡
:12
ያ ታላቂቱን እሳት የሚገባው፡፡
:13
ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም ሕያውም አይኾንም፡፡
:14
የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡
:15
የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡
:16
ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡
:17
መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡
:18
ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡
:19
በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡