86 - The Nightcommer - Aţ-Ţāriq
:1
በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ፡፡
:2
የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?
:3
ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው፡፡
:4
ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
:5
ሰውም ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፡፡
:6
ከተስፈንጣሪ ውሃ ተፈጠረ፡፡
:7
ከጀርባና ከእርግብግብቶች መካከል የሚወጣ ከኾነ (ውሃ)፡፡
:8
እርሱ (አላህ) በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው፡፡
:9
ምስጢሮች በሚገለጡበት ቀን፡፡
:10
ለእርሱም (ለሰው) ኀይልና ረዳት ምንም የለውም፡፡
:11
የመመለስ ባለቤት በኾነችው ሰማይም እምላለሁ፡፡
:12
(በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በኾነችው ምድርም፤
:13
እርሱ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ ቃል ነው፡፡
:14
እርሱም ቀልድ አይደለም፡፡
:15
እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ይሠራሉ፡፡
:16
(እኔ) ተንኮልንም እመልሳለሁ፡፡
:17
ከሓዲዎችንም ቀን ስጣቸው፡፡ ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው፡፡