85 - The Mansions of the Stars - Al-Burūj
:1
የቡርጆች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡
:2
በተቀጠረው ቀንም፤
:3
በተጣጅና በሚጣዱትም፤ (እምላለሁ)፡፡
:4
የጉድቡ ባለቤቶች ተረገሙ፡፡
:5
የማገዶ ባለቤት የኾነቺው እሳት (ባለቤቶች)፡፡
:6
እነርሱ በርሷ (አፋፍ) ላይ ተቀማጮች በኾኑ ጊዜ፤ (ተረገሙ)፡፡
:7
እነርሱም በምእምናኖቹ በሚሠሩት (ማሰቃየት) ላይ መስካሪዎች ናቸው፡፡
:8
ከእነርሱም በአላህ አሸናፊው፣ ምስጉኑ በኾነው (ጌታ) ማመናቸውን እንጅ ሌላ ምንም አልጠሉም፡፡
:9
በእዚያ የሰማያትና የምድር ንግሥና ለእርሱ ብቻ በኾነው (አላህ ማመናቸውን)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ መስካሪ ነው፡፡
:10
እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው፡፡
:11
እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችንም የሠሩ ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፡፡ ይህ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
:12
የጌታህ በኀይል መያዝ ብርቱ ነው፡፡
:13
እነሆ እርሱ መፍጠርን ይጀምራል፤ ይመልሳልም፡፡
:14
እርሱም ምሕረተ ብዙ ወዳድ ነው፡፡
:15
የዙፋኑ ባለቤት የላቀው ነው፡፡
:16
የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው፡፡
:17
የሰራዊቶቹ ወሬ መጣልህን?
:18
የፈርዖንና የሰሙድ፤ (ወሬ)፡፡
:19
በእውነቱ እነዚያ የካዱት በማስተባበል ውስጥ ናቸው፡፡
:20
አላህም በዙሪያቸው (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡
:21
ይልቁንም እርሱ የከበረ ቁርኣን ነው፡፡
:22
የተጠበቀ በኾነ ሰሌዳ ውስጥ ነው፡፡