84 - The Sundering - Al-'Inshiqāq
:1
ሰማይ በተቀደደች ጊዜ፤
:2
ለጌታዋም (ትዕዛዝ) በሰማች ጊዜ፤ (ልትሰማ) ተገባትም፤
:3
ምድርም በተለጠጠች ጊዜ፤
:4
በውስጧ ያለውንም ሁሉ በጣለችና ባዶ በኾነች ጊዜ፤
:5
ለጌታዋም በሰማች ጊዜ፤ (መስማት) ተገባትም፤ (ሰው ሁሉ ሥራውን ይገናኛል)፡፡
:6
አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ፡፡
:7
መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ፤
:8
በእርግጥ ቀላልን ምርመራ ይመረመራል፡፡
:9
ወደ ቤተሰቦቹም ተደሳች ኾኖ ይመለሳል፡፡
:10
መጽሐፉን በጀርባው ኋላ የተሰጠ ሰውማ፤
:11
(ዋ! ጥፋቴ በማለት) ጥፋትን በእርግጥ ይጠራል፡፡
:12
የተጋጋመች እሳትንም ይገባል፡፡
:13
እርሱ በቤተሰቡ ውስጥ ተደሳች ነበርና፡፡
:14
እርሱ (ወደ አላህ) የማይመለስ መኾኑን አስቧልና፡፡
:15
አይደለም (ይመለሳል)፡፡ ጌታው በእርሱ (መመለስ) ዐዋቂ ነበር፤ (ነውም)፡፡
:16
አትካዱ፤ በወጋገኑ እምላለሁ፡፡
:17
በሌሊቱም በሰበሰውም ሁሉ፤
:18
በጨረቃውም በሞላ ጊዜ (እምላለሁ)፡፡
:19
ከኹነታ በኋላ ወደ ሌላ ኹነታ ትለዋወጣላችሁ፡፡
:20
የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው?
:21
በእነርሱም ላይ ቁርኣን በተነበበ ጊዜ የማይሰግዱት፤ (ምንአላቸው?)
:22
በእርግጡ እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ) ያስተባብላሉ፡፡
:23
አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን ዐዋቂ ነው፡፡
:24
በአሳማሚ ቅጣትም አብስራቸው፡፡
:25
ግን እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩ ለእነርሱ የማይቆረጥ ምንዳ አልላቸው፡፡