ሁሉም የእስልምና ቤተ መጻሕፍት

80 - He Frowned - `Abasa

:1

ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡

:2

ዕውሩ ስለ መጣው፡፡

:3

ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡፡

:4

ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡፡

:5

የተብቃቃው ሰውማ፤

:6

አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡

:7

ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡፡

:8

እየገሰገሰ የመጣህ ሰውማ፤

:9

እርሱ (አላህን) የሚፈራ ሲኾን፤

:10

አንተ ከእርሱ ትዝዘናጋለህ፡፡

:11

ተከልከል፡፡ እርሷ ማስገንዘቢያ ናት፡፡

:12

የሻም ሰው (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል፡፡

:13

በተከበሩ ጽሑፎች ውስጥ ነው፡፡

:14

ከፍ በተደረገች ንጹሕ በተደረገች (ጽሑፍ ውስጥ ነው)፡፡

:15

በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡

:16

የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡

:17

ሰው ተረገመ፤ ምን ከሓዲ አደረገው?

:18

(ጌታው) በምን ነገር ፈጠረው? (አያስብምን?)

:19

ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነውም፡፡

:20

ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራው፡፡

:21

ከዚያም ገደለው፤ እንዲቀበርም አደረገው፡፡

:22

ከዚያም (ማንሳቱን) በሻ ጊዜ ያስነሳዋል፡፡

:23

በእውነት ያንን (ጌታው) ያዘዘውን ገና አልፈጸመም፡፡

:24

ሰውም ወደ ምግቡ ይመልከት፡፡

:25

እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መኾናችንን፡፡

:26

ከዚያም ምድርን (በደካማ ቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤

:27

በውስጧም እኽልን ያበቀልን፤

:28

ወይንንም፤ እርጥብ ያበቀልን፤

:29

የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤

:30

ጭፍቆች አትክልቶችንም፤

:31

ፍራፍሬንም ገለባንም፤ (ያበቀልን መኾናችንን ይመልከት)፡፡

:32

ለእናንተም ለእንስሶቻችሁም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን ሠራን)፡፡

:33

አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤

:34

ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤

:35

ከናቱም ካባቱም፤

:36

ከሚስቱም ከልጁም፤

:37

ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ኹነታ አልለው፡፡

:38

ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው፤

:39

ሳቂዎችም ተደሳቾችም ናቸው፡፡

:40

ፊቶችም በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትቢያ አልለባቸው፤

:41

ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤

:42

እነዚያ እነሱ ከሓዲዎቹ አመጸኞቹ ናቸው፡፡