ሁሉም የእስልምና ቤተ መጻሕፍት

79 - Those who drag forth - An-Nāzi`āt

:1

በኃይል አውጪዎች በኾኑት፤

:2

በቀስታ መምዘዝንም መዘዦች በኾኑት፤

:3

መዋኘትም ዋኚዎች በኾኑት፤

:4

መቅደምንም ቀዳሚዎች በኾኑት፤

:5

ነገርንም አስተናባሪዎች በኾኑት (መላእክት) እምላለሁ፡፡ (በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡

:6

ተርገፍጋፊይቱ (ምድር) በምትርገፈገፍበት ቀን፤

:7

ለጣቂይቱ የምትከተላት ስትኾን (ትቀሰቀሳላችሁ)፡፡

:8

በዚያ ቀን ልቦች ተሸባሪዎች ናቸው፡፡

:9

ዓይኖቻቸው ተዋራጆች (አቀርቃሪዎች) ናቸው፡፡

:10

«እኛ ወደ መጀመሪያይቱ ኹነታ ተመላሾች ነን?» ይላሉ፡፡

:11

«የበሰበሱ አጥንቶች በኾን ጊዜ (እንቀሰቀሳለን?)»

:12

«ይህቺ ያን ጊዜ ባለ ከሳራ መመለስ ናት» ይላሉ፡፡

:13

እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት፡፡

:14

ወዲያውኑም እነርሱ እንቅልፍ በሌለባት (ምድር) ላይ ይኾናሉ፡፡

:15

የሙሳ ወሬ መጣልህን?

:16

ጌታው በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ በጠራው ጊዜ፤

:17

ወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡

:18

በለውም፡- «ወደ መጥራራትህ ላንተ (መንገድ) አለህን?»

:19

«ወደ ጌታህም ልመራህ ትፈራውም ዘንድ፤ (መንገድ አለህን?)» አለው፡፡

:20

ታላቂቱንም ተዓምር አሳየው፡፡

:21

አስተባበለም፤ አመጸም፡፡

:22

ከዚያም (ለማጥፋት) የሚተጋ ኾኖ ዞረ፡፡

:23

(ሰራዊቶቹን) ሰበሰበም፤ ተጣራም፡፡

:24

አለም፡- «እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ፡፡»

:25

አላህም በኋለኛይቱና በፊተኛይቱ (ቃል) ቅጣት ያዘው፡፡

:26

በዚህ ውስጥ ለሚፈራ ሰው በእርግጥ መገምገሚያ አለበት፡፡

:27

ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? (አላህ) ገነባት፡፡

:28

ከፍታዋን አጓነ፤ አስተካከላትም፡፡

:29

ሌሊቷንም አጨለመ፡፡ ቀንዋንም ገለጸ፡፡

:30

ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡

:31

ውሃዋንና ግጦሿን ከእርሷ አወጣ፡፡

:32

ጋራዎችንም አደላደላቸው፡፡

:33

ለእናንተና ለእንስሶቻችሁ መጣቀሚያ ይኾን ዘንድ (ይህን አደረገ)፡፡

:34

ታላቂቱም መዐት በመጣች ጊዜ፣

:35

ሰው ሁሉ የሠራውን በሚያስታውስበት ቀን፣

:36

ገሀነምም ለሚያይ ሰው በተገለጠች ጊዜ፣

:37

የካደ ሰውማ፣

:38

ቅርቢቱንም ሕይወት የመረጠ፣

:39

ገሀነም እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡

:40

በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ

:41

ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡

:42

«ከሰዓቲቱ መቼ ነው መኾኛዋ?» ሲሉ ይጠይቁሃል፡፡

:43

አንተ እርሷን ከማስታወስ በምን ውስጥ ነህ?

:44

(የዕውቀት) መጨረሻዋ ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡

:45

አንተ የሚፈራትን ሰው አስፈራሪ ብቻ ነህ፡፡

:46

እነርሱ በሚያዩዋት ቀን ያንዲት ቀን ምሽትን ወይም ረፏዷን እንጅ ያልቆዩ ይመስላሉ፡፡