101 - The Calamity - Al-Qāri`ah
1
ቆርቋሪይቱ (ጩኸት)፤
2
ምን አስደናቂ ቆርቋሪ ናት!
3
ቆርቋሪይቱም ምን እንደኾነች ምን አሳወቀህ?
4
ሰዎች እንደ ተበታተነ ቢራቢሮ (ወይም ኩብኩባ) በሚኾኑበት ቀን፤
5
ጋራዎችም እንደ ተነደፈ ሱፍ በሚኾኑበት (ቀን ልቦችን በድንጋጤ ትቆረቁራለች፡፡)
6
ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ፤
7
እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፡፡
8
ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ፤
9
መኖሪያው ሃዊያህ ናት
10
እርሷም ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
11
(እርሷ) በጣም ተኳሳ እሳት ናት፡፡