ሁሉም የእስልምና ቤተ መጻሕፍት
1

በብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡

2

መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ፡፡

3

ተከልከሉ፤ ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፡፡

4

ከዚያም ተከልከሉ፤ ወደ ፊት ታውቃላችሁ፡፡

5

በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) እርግጠኛ ዕውቀትን ብታውቁ ኖሮ፤ (ባልዘናጋችሁ ነበር)፡፡

6

ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ፡፡

7

ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፡፡

8

ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ፡፡