96 - The Clot - Al-`Alaq
:1
አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡
:2
ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡
:3
አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲኾን፤
:4
ያ በብርዕ ያስተማረ፡፡
:5
ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን፡፡
:6
በእውነቱ ሰው ወሰንን ያልፋል፡፡
:7
ራሱን የተብቃቃ (ባለ ሀብት) ኾኖ ለማየቱ፡፡
:8
መመለሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡
:9
አየህን? ያንን የሚከለክለውን፡፡
:10
ባሪያን በሰገደ ጊዜ፤
:11
አየህን? ንገረኝ (ተከልካዩ) በትክክለኛ መንገድ ላይ ቢኾን፤
:12
ወይም (ፈጣሪውን) በመፍራት ቢያዝ፤
:13
አየህን? ንገረኝ (ከልካዩ) ቢያስተባብልና (ከእምነት) ቢሸሽ፤
:14
አላህ የሚያይ መኾኑን አያውቅምን?
:15
ይተው ባይከለከል አናቱን ይዘን እንጎትተዋለን፡፡
:16
ውሸታም ስሕተተኛ የኾነችውን አናቱን፡፡
:17
ሸንጎውንም ይጥራ፡፡
:18
(እኛም) ዘበኞቻችንን እንጠራለን፡፡
:19
ይከልከል አትታዘዘው፡፡ ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡