ሁሉም የእስልምና ቤተ መጻሕፍት

51 - The Winnowing Winds - Adh-Dhāriyāt

:1

መበተንን በታኞች በኾኑት (ነፋሶች)፡፡

:2

ከባድ (ዝናምን) ተሸካሚዎች በኾኑትም (ደመናዎች)፡፡

:3

ገር (መንሻለልን) ተንሻላዮች በኾኑትም (መርከቦች)፡፡

:4

ነገርን ሁሉ አከፋፋዮች በኾኑትም (መላእክት) እምላለሁ፡፡

:5

የምትቀጠሩት (ትንሣኤ) እውነት ነው፡፡

:6

(እንደየሥራው) ዋጋን ማግኘትም፤ ኋኝ ነው፤ (የማይቀር ነው)፡፡

:7

የ(ከዋክብት) መንገዶች ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡

:8

እናንተ (የመካ ሰዎች) በተለያየ ቃል ውስጥ ናችሁ፡፡

:9

ከርሱ የሚዝዞር ሰው ይዝዞራል፡፡

:10

በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ፡፡

:11

እነዚያ እነርሱ በሚሸፍን ስሕተተ ውስጥ ዘንጊዎች የኾኑት፡፡

:12

የዋጋ መስጫው ቀን መቼ እንደ ኾነ ይጠይቃሉ፡፡

:13

(እነርሱ) በእሳት ላይ በሚፈተኑበት ቀን ነው፡፡

:14

«መከራችሁን ቅመሱ፤ ይህ ያ በእርሱ ትቻኮሉበት የነበራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡

:15

አላህን ፈሪዎቹ በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡

:16

ያንን ጌታቸው የሰጣቸውን ተቀባዮች ኾነው፤ (በገነት ውስጥ ይኾናሉ)፡፡ እነርሱ ከዚህ በፊት መልካም ሰሪዎች ነበሩና፡፡

:17

ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ፡፡

:18

በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡

:19

በገንዘቦቻቸውም ውስጥ ለለማኝና (ከልመና) ለተከለከለም (በችሮታቸው) መብት አልለ፡፡

:20

በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች ምልክቶች አልሉ፡፡

:21

በነፍሶቻችሁም ውስጥ (ምልክቶች አልሉ)፤ ታዲያ አትመለከቱምን?›

:22

ሲሳያችሁም የምትቀጠሩትም (ፍዳና ምንዳ) በሰማይ ውስጥ ነው፡፡

:23

በሰማይና በምድር ጌታም እምላለሁ፡፡ እርሱ እናንተ እንደምትናገሩት ብጤ እርግጠኛ ነው፡፡

:24

የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?

:25

በእርሱ ላይ በገቡና «ሰለም» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ፤» አላቸው፡፡

:26

ወደ ቤተሰቡም ተዘነበለ፤» ወዲያውም የሰባ ወይፈንን አመጣ፡፡

:27

ወደእነርሱም (አርዶና ጠብሶ) አቀረበው፡፡ «አትበሉም ወይ?» አላቸው፡፡

:28

ከእነርሱ መፍራትንም በልቡ አሳደረ፡፡ «አትፍራ» አሉት፡፡ በዐዋቂ ወጣት ልጅም አበሰሩት፡፡

:29

ሚስቱም እየጮኸች መጣች፡፡ ፊቷንም መታች፡፡ «መካን አሮጊት ነኝ» አለችም፡፡

:30

እንደዚህ ጌታሽ ብሏል፡፡ «እነሆ እርሱ ጥበባ ዐዋቂ ነውና» አሏት፡፡

:31

«እናንተ መልክተኞች ሆይ! ታዲያ ነገራችሁ ምንድን ነው?» አላቸው፡፡

:32

(እነርሱም) አሉ፡- «እኛ ወደ አመጸኞች ሕዝቦች ተልከናል፡፡»

:33

በእነርሱ ላይ ከጭቃ የኾኑን ድንጋዮች ልንለቅባቸው (ተላክን)፡፡

:34

በጌታህ ዘንድ ለድንበር አላፊዎቹ (በየስማቸው) ምልክት የተደረገባት ስትኾን፡፡

:35

ከምእምናንም፤ በእርሷ (በከተማቸው) ውስጥ የነበሩትን አወጣን፡፡

:36

በውስጧም ከሙስሊሞች ከአንድ ቤት (ቤተሰቦች) በስተቀር አላገኘንም፡፡

:37

በውስጧም ለእነዚያ አሳማሚውን ቅጣት ለሚፈሩት ምልክትን አስቀረን፡፡

:38

በሙሳም (ወሬ) ውስጥ ወደ ፈርዖን በግልጽ ማስረጃ በላክነው ጊዜ (ምልክትን አደረግን)፡፡

:39

ከድጋፉ (ከሰራዊቱ) ጋርም (ከእምነት) ዞረ፡፡ (እርሱ) «ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነው» አለም፡፡

:40

እርሱንም ሰራዊቱንም ያዝናቸው፡፡ እርሱ ተወቃሽ ሲኾን በባሕር ውስጥም ጣልናቸው፡፡

:41

በዓድም በእነርሱ ላይ መካንን ነፋስ በላክን ጊዜ (ምልክት አልለ)፡፡

:42

በላዩ ላይ የመጣችበትን ማንኛውንም ነገር እንደ በሰበሰ አጥንት ያደረገችው ብትኾን እንጂ አትተወውም፡፡

:43

በሰሙድም ለእነርሱ «እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ ተጣቀሙ» በተባሉ ጊዜ (ምልክት አልለ)፡፡

:44

ከጌታቸው ትዕዛዝም ኮሩ፡፡ እነርሱም እያዩ ጩኸት ያዘቻቸው፡፡

:45

መቆምንም ምንም አልቻሉም፡፡ የሚርረዱም አልነበሩም፡፡

:46

የኑሕንም ሕዝቦች ከዚህ በፊት (አጠፋን)፡፡ እነርሱ አመጸኞች ሕዝቦች ነበሩና፡፡

:47

ሰማይንም በኀይል ገነባናት፡፡ እኛም በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡

:48

ምድርንም ዘረጋናት፡፡ ምን ያማርንም ዘርጊዎች (ነን!)

:49

ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት (ተቃራኒ) ዓይነትን ፈጠርን፡፡

:50

«ወደ አላህም ሽሹ፤ እኔ ለእናንተ ከርሱ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና» (በላቸው)፡፡

:51

ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አታድርጉ፡፡ እኔ ለእናንተ ከእርሱ (የተላክሁ) ግልጽ አስፈራሪ ነኝና፡፡

:52

(ነገሩ) እንደዚሁ ነው፡፡ እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልክተኛ ማንም አልመጣቸውም፡፡ (እርሱ) «ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነው» ያሉ ቢኾኑ እንጂ፡፡

:53

በእርሱ (በዚህ ቃል) አደራ ተባብለዋልን? አይደለም፤ እነርሱ ጥጋበኞች ሕዝቦች ናቸው፡፡

:54

ከእነርሱም (ክርክር) ዘወር በል፤ (ተዋቸው)፡፡ አንተ ምንም ተወቃሽ አይደለህምና፡፡

:55

ገሥጽም፤ ግሣጼ ምእመናንን ትጠቅማለችና፡፡

:56

ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡

:57

ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም፡፡

:58

አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው፡፡

:59

ለእነዚያም ለበደሉት እንደ ጓደኞቻቸው ፋንታ ብጤ (የቅጣት) ፋንታ አልላቸው፡፡ ስለዚህ አያስቸኩሉኝ፡፡

:60

ለነዚያም ለካዱት ከዚያ ከሚቀጠሩት ቀናቸው ወዮላቸው፡