ሁሉም የእስልምና ቤተ መጻሕፍት

107 - The Small kindnesses - Al-Mā`ūn

1

ያንን በምርመራው የሚያስተባብለውን አየህን? (ዐወቅከውን?)

2

ይህም ያ የቲምን በኀይል የሚገፈትረው፤

3

ድኻንም በማብላት ላይ የማያግባባው ሰው ነው፡፡

4

ወዮላቸው ለሰጋጆች፡፡

5

ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)፡፡

6

ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት፡፡

7

የዕቃ ትውስትንም (ሰዎችን) የሚከለክሉ ለኾኑት (ወዮላቸው)፡፡